የእምነት አቋም
1-መጽሐፍ ቅዱስ (66 መጽሐፍት) ትክክለኛ እና እውነተኛ እንዲሁም የማይለወጥ የእግዚአብሔር አስትንፋሳዊ ቃል እንደሆነ እናምናለን፡፡ ስለሆነም ብቸኛ የእምነት እና የሕይወት የመጨረሻ ሥልጣን አለው። ምሳሌ 30:5-6፤ ኢሳይያስ 8:20፤ ዮሐንስ 10:35፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16-17፤ 2 ጴጥሮስ 1:21
2-እግዚአብሔር በአንድነትና በሶስትነት ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር አምላክ እንደሆነ፤ በመለኮት አንድ ሲሆን በአካል ሶስት እንደሆነ እናምናለን (አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ)፡፡ ዘዳግም 6:4፣ ማቴዎስ 28:19፣ ዮሃንስ 14:26፣ 2 ቈረንቶስ 13:14፡
3-እግዚአብሔር አብ አባት ሲሆን ሁሉን የሚችልና ሁሉን የሚገዛ ዘላለማዊ አምላክ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡
7-ኢየሱስ ከድንግል እንደተወለደና ለአብ ፈጽሞ እንደታዘዘ እናምናለን፤ እንዲሁም ድንቅና ተአምራትን እንዳደረገ፣ በመስቀል ላይ እንደ ሞተ፣ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሳና ወደ ሰማይ አርጎ በሁሉ ላይ እንደ ነገሰ እናምናለን። ሉቃስ 1:26-35፣ እብራውያን 4:15፣ ዮሃንስ 14:11፣ ሉቃስ 23-24፣ ኤፌሶን 1:20-23
9-ሰው በኃጢአት እንደ ወደቀና እራሱን ማዳን እንደማይችል እናምናለን። ዘፍጥረት 3፣ ሮሜ 3:12, 23፣ ሮሜ 5:12
10-መዳን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለሆነ በክርስቶስ በማመን ምንቀበለው እንጅ በስራ እንደማናገኘው እናምናለን። ዮሃንስ 3:16፣ ሮሜ 1:16-17፣ ገላትያ 2:16-21
11-መንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደት እንደሰጠንና ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል እንዳደረገን፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደሚያረጋግጥልን፣ ወደ እውነት እንደሚመራን፣ በጸጋ ስጦታዎቹ እንደሚያስታጥቀንና ኃይል እንደሚሰጠን እናምናለንል። ዮሃንስ 3:3-8፣ ግብሪ ሃዋርያት 1:8፣ ሮሜ 8፣ 1 ቈረንቶስ 12፣ ገላትያ 5:16-26፣ ኤፌሶን 3:16-21
12- ቤተ ክርስቲያን በዘመናት መካከል ከሕዛብ ሁሉ በክርስቶስ የተጠሩ ሰዎች ህብረትና የክርስቶስ አካል እንደሆነች እናምናልን። ሮሜ 12:5፣ ገላትያ 3:26-29፣ ኤፌሶን 1:22-23፣ ራእይ 7:9
13-ዳግም የተወለደ አማኝ ሁሉ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም በውኃ በመጠመቅ ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር መተባበሩን እንዲሁም ለኃጢአት ሞቶ ለጽድቅ መነሳቱን መግለጽ እንዳለበት እናምናለን።ማቴዎስ 28:18-20
14-ዳግም የተወለደ አማኝ ሁሉ የጌታ እራትን በመካፈል ጌታ ዳግም እስኪመጣ ሞቱንና ትንሳኤውን እንዲሁም ከአማኞች ጋር ያለውን ኅብረት መግለጽ እንዳለበት እናምናለን፡፡ማቴዎስ 26: 26-28
20-እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅድስና ሕይወት እንድንመላለስ እግዚአብሔር እንደ ጠራን እናምናለን። መዝሙር 24:1፣ ቈሎሴ 3:17፣ 2 ቈረንቶስ 10:5