We envision that every fellow member will be equipped with the word and the Spirit of God. So we are dedicated to frequent prayers, Bible study, teaching, and brotherhood relationships. You can reach out and connect with us by sending an Email to Kingdom Community Ministry.
ኪንግደም ኮሙኒቲ ሚኒስትሪ እግዚአብሔር በሰጠን ራዕይ እና ተልዕኮ ዓለምን በወንጌል ለመድረስ እና አማኙን ማኅበረሰብ በእግዚአብሔር ቃል ለማስታጠቅ የተመሰረተ መንፈሳዊ ሚኒስትሪ ነው። ሚኒስትሪው አማኞች እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ እንዲሁም ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለማድረስ ከቤተክርስትያን ጋር ይሰራል፡፡
በመሆኑም እግዚአብሔር የሰጠንን አገልግሎት በትጋትና በታማኝነት በማከናወን የእግዚአብሔር መንግስት በምድራችን ብሎም በዓለም ላይ እንዲሰፋ እጅ ለእጅ ተያይዘን እናገለግላለን። አማኙ ማኅበረሰብ ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲታጠቅ በትጋት እናገለግላለን። ስለሆነም ለጸሎትና ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ ለመማርና ለማስተማር እንዲሁም ለወንድማማች ፍቅር እንተጋለን። በኪንግደም ኮሙኒቲ ሚኒስትሪ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኜትና አብሮ ለማገልገል ኪንግደም ኮሙኒቲ ሚኒስትሪ ብለው ይጻፉልን።
Comments
Post a Comment